November 4, 2024

Custom

በኤርፖርት ጉምሩክ አንዲት የአረብ ሀገር ተመላሽ ባጋጠማት ጉዳይ ቤተሰቦቿ አንድ መልዕክት ልከዋል።

ግለሰቧ አሁን ላይ በእስር ላይ የምትገኝም ሲሆን ከቀናት በፊት የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባት እያተጠባበቀች ነው።

ቲክቫህ በጉዳዩ ላይ ምንም እንኳን ከኤርፖርት ጉምሩክ ምላሽ ባያገኘም ዋናው መስሪያ ቤት ግን አስተያየቱን ተቀብሏል።

ጉዳዩ ምንድነው ?

(የቤተሰቦቿ ቃል ቃል በቃል የቀረበ)

" እህታችን ከአረብ ሀገር ተመላሽ ናት።

የስደት ኑሮ በቃኝ ብላ በመወሰኗም ወደ ሀገር ቤት ተመልሳለች።

መንግሥት ከአረብ ሀገር ለሚመለሱ ዜጎች ባመቻቸው ዕድል የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቅማ ከ1 ወር በፊት የኪችን እቃዎችና ሌሎች የሚያስፈልጋትን እቃዎች አስገብታለች።

ልክ እንዳስገባች በተቀመጠው አሰራር ' የቀረኝ እቃ አለ ' ስትል የቀረውን እቃ ማህተም አስመትተሽ ይዘሽ ስትገቢ በሱ መሰረት ትስተናገጃለሽ ትባላለች።

ይሄን የቀራትን እቃ ይዛ ትመጣለች። ይዛ ስትመጣም ፥ ' መክፈል አለብሽ ' ትባላለች።

ይህች እህት በውጭ ሀገር በምትሰራበት ወቅት እግሯ ላይ የጤና ችግር ስላለባት እዛ ቦታ ጊዜ ማጥፋት ስላልፈለገች ክፍያውን ትከፍላለች።

ክፍያውን ከፍላም ፣ የጉርምሩክ ፣ የኢቲ ሂደቶችን አጠናቃ ይዛ ወጣች። ልክ መኪና ላይ ስትጭን የጉምሩክ ኢንተለጀንት የሚባሉት ይመጡና ' እንዳይጫን ' ብለው ያስቆማሉ።

ከዛም ዶክመንቷን ጠይቀው ' ትፈለጊያለሽ ' ብለው ወደ አንድ ክፍል ይዘዋት ይገባሉ።

በኃልም የጉምሩክ ሰዎቹ ፌዴራል ፖሊስ ያስጠሩና ' እቃው ያንቺ አይደለም እመኚ ' የሚል ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ።

' እቃው የኔ አደለም ብለሽ ብታምኚ እንለቅሻለን ፤ ባታምኚ ደግሞ ትታሰሪያለሽ ' የሚል ማስፈራሪያ መናገር ይጀምራሉ።

ክፍሉ ውስጥ ካሜራ አለ። ያደረጉትን ሁሉ በካሜራው ማየት ይቻላል።

ከዛም ስልኳን ይቀሟትና ወስደው ፓተርኑን አስከፍተው ይመጣሉ። ስልኳ ውስጥ ከሌሎች ሰዎች ጋር ትጻጻፍ እና ታወራ የነበረውን መስማት ይጀምራሉ።

ከዛ እነዚሁ የጉምሩክ ሰዎች ' እቃው ያንቺ አይደለም የሰው ነው። ካመንሽ እንለቅሻለን ፤ ካልሆነ ትታሰሪያለሽ። ከምትታሰሪ እመኚና እንልቀቅሽ እያሉ ' ሲያስፈራሯት ' እሺ የሰው ነው ' የሚል ምላሽ ትሰጣለች።

ከዛም ፓስፖርቷን ተቀብለው አንደኛው ደብዳቤ ጻፊ ይላታል። የምትፅፈውንም እሱ እራሱ ነው የሚነግራት። ካፃፏት በኃላ ፈርሚ አሏት። እሷም " አልፈርምም ፤ የምትሉኝን ነገር አልፈርምም " ትላለች።

በኃላም እኛ እንደውልልሻለን ብለው ቀጠሮ ቀጥረዋት ይለቋታል።

ተመልሳ በማግስቱ በቀጠሮዋ መሰረት ትሄዳለች። ከዛም ' ድጋሚ ፍተሻ ይደረግና ጨራርሰሽ ይዘሽ ትሄጃለሽ ' ትባልና ፍተሻ ተደረገና በማሽንም በሰውም እያንዳንዱ እቃም ታየ።

በቃ እከሌ ጋር ሂጂ እከሌ ጋር እያሉ ማጉለለት ያዙ። አርብ ከጥዋት እስከማታ እንዲሁ እዛው ስትንከራተት ቆይታ ተመለሰች።

ቅዳሜ ደግሞ ያኛው ሺፍት የለም እያሉ ሲያጉላሉ ቆይተው ሰኞ በጥዋት እንድትመጣ ትቀጠራለች። እቃሽን ትወስጃለሽ ትባላለች።

ሰኞ ባለፈው ሳምንት ሄዳ የጉምሩክ ደህንነት ክፍል ስትገባ የነበረው ሰው ' እኔ ጨርሼ አስተላልፊያለሁ ' ይላታል። ከዛ ሌላ ኃላፊ ጋር ገብታ ስታናግር ' እየዋሸሽ ነው አላምንሽም ' ይላታል። እሷም ሁኔታውን ስታስረዳው ብትቆይም ሊቀበል ፍቃደኛ አልሆነም።

ህግ ክፍል ትመራና ትሄዳለች። እዛ ያለው ሰው ' ስራ ይዣለሁ አሁን አላናግርሽም ውጪ ' ይላታል። አመነጫጭቆ እንድትወጣ ይነግራታል። 30 ደቂቃ ጠብቃ ተመልሳ ስትጠይቀው ' ሴትዮ አትሰሚኝም የምላሽን ' ብሎ በኃይል ሲናገራት ' ወዴት ነው መሄድ ያለብኝ ? ' ብላ ትጠይቃለች እሱም ' ወደምትፈልጊበት ሂጂ ' የሚል መልስ ይሰጣል።

ተመልሳ ስትገባ ግን ተረጋግቶ አናገራት። መፍትሄ የለውም ወይ ጉዳዬ ? ስትል ' መፍትሄ አለው እቃሽ እየተዘጋጀ ነው ' ይላታል።

እዛው እሷን ቁጭ አድርጎም ስልክ ደውሎ ' ወረቀቱ ተዘጋጅቷል ? አምጡልኝ ! ሁለት ሰዎችም ላኩልኝ ' ብሎ ተናገረ።

በዚህ መኃል ግን እያናገራት ነበር ' ስራ እንዴት ነው ? ምን ልትሰሪ ነው ? ዱባይ ስንት ይከፈልሽ ነበር ? ' የሚሉ ጥያቄዎችን እየጠየቀ ትመልስለት ነበር።

በኃላ የተጠሩት ሰዎች ሲደርሱ ነገሮች ተቀየሩ። ያመጡት ወረቀት ላይ ' ፈርሚ ' ትባላለች። አንብቢ ተብላ ካነበበች በኃላ ' እኔ ኮንትሮባንድ እቃ አላስገባሁም ፤ እቃም ለሰው አለመጣሁም እቃውም የራሴ ነው አልፈርምም ' ትላቸዋለች። የመጡት ሰዎች በግድ ጉልበት ተጠቅመው አስፈረሟት።

ከዛም አሰሯት። ወደ ማቆያ ክፍልም አስገቧት። ለቤተሰብ አሳውቂ ተብላም ቤተሰብ ሄዶ ጠየቃት። ፍርድ ቤት ትቀርቢያለሽም ተብላለች።

በእቃዋን ሲፈትሹ ከነበሩት ሰዎች መካከል ' ኤክስሬይ ድጋሚ ከተፈተሸ በኃላ ጨርሰሻል ነገ ይዘሽ ትወጫለሽ ' ሲሏት ነበር። እንደዚህ ያሉትን ሰዎች ከታሰረች በኃላም በሰው በሰው ሲጠየቁ ' ትለቀቃለች ልዩነት ካለ ትከፍላለች እንጂ ምንም ነገር የለም። ' የሚል መልስ ነው የሰጡት።

እንደተሰማው ከሆነ ካሜራ በሶፋ መሀል ይዞ የገባ ሰው ነበር። ያኛው ይዞ ወጥቷል ነው ነገሩ። በመመሳሰል ነው የተያዘችው የሚል ነገር ከያዟት ሰዎች ውስጥ ነግሯታል።

እነዛን ሰዎች ይዘናል ብለው ነው ይህን ያህል ሲያጉላሏት ቆይተው እሷም ሶፋ ስላስገባች በኃላ ወደ እስር ያመሩት።

እያንዳንዱ ነገር ግን ተፈትሾ፣ አስፈላጊውን ነገር አሟልቶ ነበር ሲያልፍ የነበረው።

ግማሹ ' ትወጫለሽ ' ግማሹ ' ቆይ እየታየ ነው ' እያለ ሳምንት ሙሉ ሲያመላልሷት ነበር ያውም ሆቴል ይዛ። ከዚህ በኃላ ነው ወደ እስር የገቡት። "

ጉምሩክ ኮሚሽን ምን አለ ?

ን ምላሽ ሰጡ?

ኤርፓርት ጉምሩክ ቅ/

ምን ምላሽ ሰጡ?

"በጣም በርካታ መንገደኞች ከመኖራቸው አኳያ እያንዳንዱ ስፔስፊክ ጉዳይ ሄድ ኦፊስ ላይ መጥቶ የምናይበት አግባብ ባለጉዳይ መጥቶ አፒል እስካላለ ድረስ ሄድ ኦፊሱ መረጃ የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው።መሬት ላይ ያሉት አሰራሮችን ክትትል ከማድረግ አኳያ ግን ኮሚሽኑ የራሱ አሰራር አለው። የክትትል የግምገማ ስርዓቶች አሉ። ሥራዎች እንዴት እየተሰሩ ነው? የሚለውን በአኣልም ወርዶ (ከፍተኛ ኃላፊዎችን ጨምሮ) ክትትል የሚደረግባቸው አግባቦች አሉ።በዚያ ግን ሁሉንም ኢንሲደንት ካፕቸርድ ማድረግ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው።እቃው የኔ አይደለም እያለች ከሆነ፣ የሷ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ‘ይሄ እቃ የአንቺ ነው’ ብለው አስገድደውኛል የሚል ነገር ካለ ማዬት ይቻላል።ባለሙያዎችን ምንድን ነው የተፈጠረው ነገር ብሎ? ቼክ ማድረግን ይጠይቃል" ነው ያሉት።

ግለሰቧ የደረሰባትን መጉላላት፣ የ‘እቃሽ ይወረሳል’ ጉዳይና የደረሰባትን ዝርዝር ቅሬታ በመግለጽ፣ እንዲህ አይነት ድርጊት መፈጸም ለምን አስፈለገ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄም ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“እንዲህ አይነት ኢንሲደንቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ተመላሽ ኢትዮጵያውያን የሚስተናገዱባቸው በግልጽ የተቀመጡ አሰራሮች አሉ።  ለዚህ ስፔስፊክ ጉዳይ ላይ ምንም መረጃ የለኝም። በዬቀኑ በርካታ ተመላሾች/መንገደኞች ናቸው የሚስተናገዱት።ነገር ግን ማለት የምችለው ነገር፦ ‘ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ‘ውሳኔ አሰጣጥ ላይ በድሎኛል፤ ትክክለኛ ውሳኔ አልተሰጠኝም፤ በእቃዬ ላይ አላግባብ ውርስ ፈጽሞብኛል’ የሚል ቅሬታ ካላት በሕግ የተሰጣት መብት አለ። ዋናው መስሪያ ቤት መጥታ አፒል የማድረግ ማለት ነው።ስለዚህ እቃዬ አላግባብ ተወርሶብኛል የሚል ቅሬታ ካላት ኮሚሽኑ በዘረጋው የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት መሠረት 10ኛ ፎቅ ላይ፣ ውሳኔ በተሰጣት 15 ቀናት ውስጥ መጥታ አቤቱታዋን ማቅረብ ትችላለች።ከወንጀል አኳያ ያለው ጉዳይ ደግሞ በሚመለከተው አካል ነው የሚታየው። ወንጀል ተፈጽሟል? የሚል ጭብጥ ተይዞ ከሆነ የሚመለከተው የኮርት ዲቪዢን ብሎም የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚመለከተው ነው የሚሆነው” ብለዋል።

እቃውን የማታስገባበት የጊዜ ገደብ አልፎ፣ ከሚፈቀደው እቃ ውጪ አምጥታ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያም መጀመሪያ ላይ እቃው ያልፋል ተብላ መቀረጥ የሌለባት ሆኖ ሳለ ቀረጥ ከፍላለች፣ በኋላም እቃው ሊጫን ሲል ነው እንደገና ‘አይጫንም’ የተባለችው። ለዚህ የዳረጋት የእቃው አይነትና የእቃው ዘግይቶ መምጣት ሊሆን ይችላል እንዳንል ካሳለፉት በኋላ ነው የተከለከለችው፤ የኮሚሽኑ ምላሽ ምንድን ነው? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ምን ምላሽ ተሰጠ?

“ይሄ ጉዳይ ሕገ ወጥ ተግባር ተፈጽሞበታል (ከሕግ አግባብ ውጪ እቃው ሊወጣ ነው/ወጥቷል) ተብሎ ከታሰበ በጉምሩክ ግቢ ባለበትም፤ ከወጣም በኋላ እቃው ሊያዝ የሚችልበት እድል አለው።የተለያዩ የሥራ ክፍሎች አሉ። ስፔሲፊክ ስራውን የሚሰሩ ይኖራሉ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ ቼክ የሚያደርጉ አሉ። ልክ እንደኦዲት ቼክ የማድረግ ሥራ ይሰራል። የተሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው? ወይስ አይደለም? ተብሎ። መረጃው የደረሰው ዘግይቶ ከሆነ እቃው መኪና እየተጫነ ባለበት ሰዓት ላይ ሊወርድ የሚችልበት እድል ይኖራል። አንድ ኦፊሰር ውሳኔ ሰጠ ማለት የመጨሻ ላይሆን ይችላል። ስህተት ከሆነ ሊቀለበስ የሚችልበት እድል ይኖራል።ይሄ በደንበኞች ላይ መጉላላት ሊፈጥር ይችላል ትክክል ነው። ግን በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ ቼኽ የማድረጉ ሥራ በተጨባጭ መረጃ ላይ መሆን አለበት።ውሳኔው ትክክል ነው? አይደለም? የሚለው ቢመረመር ነው የሚሻለው። በኮሚሽኑ አሰራር መሠረት ብትሄድ የተሻለ ነው፣ ከዛ ውጫ ግን እንደ ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ደረሰባት እንግልት ካለ በኮሚሽኑ ስም ይቅርታ እንጠይቃለን።ከትሪትመንት አኳያ ኦፊሰሮች፣ ባለሙያዎች፣ ኃላፊዎች በማወቅም ባለማወቅም የፈጽሙት የማስገደድ..ሌላም ሁኔታ ካለ እሱ መስተካከል ያለበት ነገር ሊሆን ይችላል” ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia