wiseholyfathers
@rafato_el
4 posts

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ንጉሡ መልኳ (ሥነ ላህይዋ) ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ። እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ከቆዩ በኋላ ንጽሕት ቅድስት አርሴማ እናታችንን በአንድ በሮሜ ባለ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር አገኟትና ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። ብፅዕት እናታችን ቅድስት ንጽሕት መርዓተ ክርስቶስ ቅድስት አርሴማም ሥነ ላህይዋ እጅጉን ልዩ የሆነ መልከ መልካም ነበረች።

በአታ ለ ማርያም

ቅድስት ድንግል ማርያም በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም ከሐና እና ከኢያቄም በፈቃደ እግዚአብሔር ተወልዳ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የኖረችው በወላጆቿ ቤት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸውን አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሰጧት፤ ካህኑ ዘካርያስም ስለምግቧ በመጨነቁ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ታጥቆ እጅ ነስቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ ከስምዖን ጀምሮ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም በተራ ቢሞክሩ በተመሳሳይ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው ሐና እና ኢያቄም እንዲቀርቡ አደረጓቸው፤ ለእነርሱም ራቀባቸው፤ ዘካርያስም ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› ባላት ጊዜ ቅድስት ማርያም ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱም ሕዝቡም የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር ብለው አስገቧት፤ይህም ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡

ምን ፍሬ አፈራን?

በ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ | ከሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሃፍ የተወሰደ | ትርጉም ገብረ እግዚአብሄር ኪደ

ጾም

ከሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሃፍ የተወሰደ ......... በ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርá‰